የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግረም ህብረ-ብሄራዊነትንና አብሮነትን ይበልጥ በማጎልበት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግረም ህብረ-ብሄራዊነትንና አብሮነትን ይበልጥ በማጎልበት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው፡፡

የተከበሩ ዶ/ር ደመቀ አጭሶ

 

ኅዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም(ሰላም ሚኒስቴር) በ5ተኛው ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ 6 ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናቸውን ጨርሰው የተመረቁ ሲሆን በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ 1ሺህ 300 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

 

በፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባልና የዕለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩ ዶ/ር ደመቀ አጭሶ የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት መርሃ-ግብር ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና መርሆችን ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በሌሎችም ማንነቶች ላይ መሠረት አድርጎ ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ የወጣቶችን የሀገር እና የሕዝብ ፍቅር ለማሳደግ ሚናው የጎላ ስለሆነ ለሀገራችን በእጅጉ አስፈላጊ ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮግራም ለወጣቶች የተለያዩ መንገዶችንና እድሎችን ከራሳቸው አልፈው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበት አቅጣጫ በማሳየት የሥራ ፈጠራ ክህሎትን እንዲያዳብሩም ቀላል የማይባል ጠቀሜታዎች ስላሉት ወጣቱ በትምህርት ያገኘውን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር አሳድጎ ለራሱና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻውን አዎንታዊ ጠጠር ማበርከት እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በበኩላቸው የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት አንዱ የሌላውን እሴቶችንና ባህል እንዲያውቅና እንዲያከብር ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡ ከጭፍን ጥላቻ ወጥቶ እርስበርስ የተጋመዱ ማህበረሰቦች እንዲፈጠሩ በማድረግ ዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ማሳደግ ካለው ፋይዳ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን የሚያሳድጉ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የሚያመጡ፣ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች እንዲሰሩ ለማድረግ አዎንታዊ ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ከናንተ ብዙ የሚማሩ በብዙ የሚያተርፉ በርካቶች ናቸውና ሀገራችሁ የሰጠቻችሁን ሀላፊነት እና የዜግነት ግዴታችሁን በሙሉ ኢትዮጵያዊ ልብ እንድትተገብሩ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም የቀጣይ አቅጣጫ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኞች በየተሰማራችሁበት አካባቢ የሰላም መልዕክተኞች በመሆን አንድነትንና ፍቅርን በተግባር ማሳየትና ማስተማር ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ይህ ፕሮግራም ሀገራችሁን ለማወቅ ወርቃማ እድል በመሆኑ ይህንን ጊዜ ሳታባክኑ በመጠቀም የተሰጣችሁን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ እንድትሰሩ አደራ ብለዋል፡፡