የዓድዋ ድል ታሪክ ለኢትዮጵያዊያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸና፣ የሉዓላዊነት፣ የአብሮነትና የሰላም መሰረት ነው
የዓድዋ ድል ታሪክ ለኢትዮጵያዊያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸና፣ የሉዓላዊነት፣ የአብሮነትና የሰላም መሰረት ነው
የአድዋ የድል ታሪክ ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸና፣ የሉዓላዊነት፣ የአብሮነትና የሰላም መሰረት ነው፡፡
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ታሪካዊ የድል አድራጊነት ገድል የፈጸሙበትና ለዓለም ህዝቦች ከጭቆናና ከባርነት ለመላቀቅ መሰረት የጣሉበት ነው፡፡
ይህ ዘመን ተሻጋሪ የድል በዓል ዘንድሮ 129ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያዉያን የወል ታሪክና ትርክት ማጠንጠኛ ዓርማ መሆኑን ሕዝቡን ማስገንዘብንና ለተጨማሪ የወል ድሎች ተነሳሽነት መፍጠርን አላማ አድርጎ ይከበራል፡፡
በዓሉን ስናከብር የቀድሞውን በመዘከር ብቻ ሳይሆን ነገን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠርና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በመረባረብ ጭምር መሆን እንዳለበት ጥሪያችንን እያስተላለፍን በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንም የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያንም እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡