የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅሞች 

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአገራዊ  የጋራ ማንነቶች፣ ጥቅሞችና እና እሴቶች ላይ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መሰረት መሆኑን በመረዳት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

እንደ ሀገር በሁሉም ነገር ላይ መግባባት ላይ መድረስ ባይጠበቅብንም  በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረስ እና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለይቶ ማወቅ ግን ለዘላቂ ሰላማች እና  አንድነታችን መሰረት ነው፡፡

ብሔራዊ ጥቅሞቻችን  ከታሪካችን፣ ከሕገ-መንግስቱ፣ የውጭ ግንኙነት/ጉዳይ ሰነዶች፣ ከተለያዩ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ሰነዶች፣ ሀገራችን ላይ አሁን እየታየ ካለው ነባራዊ ሁኔታ እና የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ እንፃር በመነሳት ‘’የኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም’’  የሚከተሉት ጉዳዮችን ይዟል፦

1.  ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ
     ---------------------------------------
ሰላምና ደህንነት በሌለበት ስለ ዘላቂ ልማት ማሰብ አይቻልም፡፡ ሰብዓዊና ቁሳዊ ልማት ማሰብ የሚሳካው በሰላም አውድ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የህግ የበላይነትንና ፀጥታን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ለሁሉም ነገሮች ስኬት መሰረት በመሆኑ የብሄራዊ ጥቅማችን አካል ነው። 

2. ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት
     -----------------------------------
ብዙ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች አሉብን በሌላ በኩል ደግሞ ሁለተናዊ ብልፅግና እንፈልጋለን፡፡ ፈተናዎቹን ለማለፍና ፍላጎታችንን ለማሳካት የብዝሃነት እና የአንድነትን ሚዛን በመጠበቅ የምንፈጥረው ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን በመሆኑ የብሄራዊ ጥቅማችን ዋነኛው አካል ተደርጎ መስራት ያስፈልጋል። 

2.  የተቋም ግንባታ
      ----------------------
በመርህ እና በእሴት የተሰናሰሉ ተቋማትን መገንባት የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገን ትውልድ ጥቅም ማስከበር ነው፡፡ ስለዚህ ተቋማትን የመገንባት ስራዎች የብሄራዊ ጥቅምን የማስከበር ስራዎች አካል ናቸው። በፖለቲካ ለውጥና አለመረጋጋት ውስጥ ባለች አገር ውስጥ የሚደረግ የአገር ግንባታ ስራዎች ቅድሚያ የሚሰጠው የተቋም ግንባታ ነው፡፡ ይህም የሀገር ሰላምና ደህንነት ላይ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ስላለው የብሄራዊ ጥቅም አካል ነው።

4. ሉአዓላዊነት 
    ----------------
አንድ ሀገር ሁለንተናዊ ፍላጎት ማሳካት የሚቻለው በነፃነት መወሰን ሲችል ብቻ ነው፡፡ ሉዓላዊነት የሌለው ሕዝብ ለሌሎች አካላት ፍለጎት የተገዛ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ/ማስጠበቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው።

5. ግብርና
     ----------
የሚመግብህ ይቆጣጠርሀል የሚባል አባባል አለ፡፡ በምግብ ራስን መቻል የነፃነት አንዱ ምሶሶ ነው፡፡ በሌሎች ሀገሮች የሚረዳ  ሀገር  በሌሎች ዘንድ ክብር ሊኖረው አይችልም፡፡ ስለዚህ ግብርናም ቁልፍ የሀገር ጥቅም ጉዳይ ነው፡፡ 

6. አረንጓዴ አሻራ
    -------------------
የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ስጋት ሆኗል፡፡  ከኢትዮጵያ አንፃር ሲታይ ደግሞ አደጋው እጅግ ይከፋል ህዝባችን በድርቅና በጎርፍ በተደጋጋሚ የሚጠቃ በመሆኑ ዛፎችን መትከልና መንከባከብ ቁልፍ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው፡፡

ይቀጥላል…
                                                                                                                        
                   ሰላም ለኢትዮጵያ!