''ሰላም  ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የሰላም ሩጫ በሰላም ተጠናቋል

Ethiopian Date

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

null ''ሰላም  ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የሰላም ሩጫ በሰላም ተጠናቋል

ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም. መነሻውን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በማድረግ በባምቢስ ፣ በዑራኤል አደባባይ ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ  መጨረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው የሰላም ሩጫ ተጠናቋል።

በሰላም ሩጫው ላይ ክቡራን ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የውጭ ሁገር ዲፕሎማቶችና አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና የኃይማኖት አባቶች በሰላም ሩጫው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የሰላም ሩጫው ዓላማ በሀገራችን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም የበለጠ እንዲያጠናክር  ለማድረግ እና መላው ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሰላም በጋራ እንዲሰሩ መነሳሳትን ለመፍጠር  ያለመ  ከመሆኑም ባሻገር እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም  የምንሰጠውን ዋጋና ለሰላም ያለንን ፍላጎት  ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ መሆኑን ተገልጿል።

በሩጫው በሴቶች እና በወንዶች ተወዳድረው 1-3 ላሸነፉ አትሌቶች ሽልማት ተበርክቶላቸል።

በመጨረሻ ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በኩል ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የሰላም ሩጫው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በተመረጡ ከተሞች ተካሂዷል።

Asset Publisher

ቪዲዮ ዜና

በይፋ የተመሰረተው የሰላም ም/ቤት ምን ሚና ይኖረዋል ?
የምሁራን ሚና ለዘላቂ ሠላም
ማህበራዊ ሚዲያ ለሰላም ግንባታ ያለው ሚና
ሚዲያ ለሰላም ሰላም ሚኒስቴር