''የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላማችን''  በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ ተካሄደ 

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 26/2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ''የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላማችን '' በሚል መሪ ሃሳብ ከሁሉም ቤተ ዕምነቶች ከተውጣጡ የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ ከኃይማኖት አስተማሪዎች፣ ፣ከፌዴራልና የክልል አመራሮች ጋር ሀገር  አቀፍ ኮንፍረንስ አካሂዷል።

ኮንፍረንሱ በኃይማኖት አባቶች የበላይ ጠባቂዎች ፀሎት እና ቡራኬ ተጀምሯል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በኮንፍረንሱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም  ሁሉም ኃይማኖቶች በአንድ ጉዳይ ላይ ይስማማሉ ይህም ''ሰላም'' በሚለው ፅንሰ ሃሳብ ነው ያሉ ሲሆን የኃይማኖት አባቶች ሰዎች ከራሳቸው፣ ከፈጣሪያቸው እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም እንዲኖሩ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ዜጎች ኃይማኖታቸውን በነፃነት ማራመድ የሚችሉት ሰላም ሲኖር ነው ያሉት ክቡር አቶ ብናልፍ  የዛሬው ውይይት ዓላማም የሀገራችንን ሰላም ለማስጠበቅ እና ብሔራዊ መግባባት ከማጎልበት አንፃር የኃይማኖት ተቋማት ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ምክክር በማካሄድ  የጋራ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ ''የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም'' የሚል ፅሁፍ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ በሆኑት በዶ/ር አወቀ አጥናፉ እንዲሁም  ''የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ልምድና ተሞክሮ '' የሚል ፅሁፍ ደግሞ የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ በሆኑት በፖስተር ታምራት አበጋዝ በኩል ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የኃይማኖት አባቶች በበኩላቸው ያለችን አንዲት ሀገር እንደመሆኑ መጠን የሀገራችን ሰላም ያሳስበናል ያሉ ሲሆን የሀገራችንን ህመም በቅጡ ተረድተን  ለመፍትሄውም ተባብረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል። አክለውም  ሰላምን የምናቀርበውም  ሆነ የምናርቀው ራሳችን እንጅ ሰላም እኮ ከጎናችን ነው ያለው ያሉ ሲሆን ሰላም ከሌለ ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ  ተቋማት ህልውናቸው አደጋ ውስጥ ይሆናል ብለዋል።

ምርጫችን ሰላም ከሆነ ሰላም እንሆናለን፣ ምርጫችን ግጭት ከሆነ ሰላማችንን እናጣለን፣ ምርጫችንን ማስተካከል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

ውይይቱን የመሩት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ የኃይማኖት ተቋማት  በውስጣቸው የሚከሰቱ ችግሮችን በራሳቸው እንዲፈቱ እና በሐይማኖቶች መካከል መከባበር እንዲኖር ሊሰሩ ይገባል ያሉ ሲሆን፣ የሰላም ሚኒስቴር የኃይማኖት ተቋማትና መንግሥት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንዲሰሩ እና የኃይማኖት ተቋማት በሰላም ግንባታ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የኃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂዎች፣ የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሁሉም የሐይማኖት ተቋማት የተወጣጡ የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከፌዴራል እና ከክልል የተገኙ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።