የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚኒስትሩ በሰላም ግንባታና በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አዲስ ከተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጋር በተደረገው የትውውቅ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፦ መጅሊሱን ለመጎብኘት ሚኒስትሩ መምጣታቸው በራሴ እና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሙስሊሙን አንድነትና የሀገራችንን ሰላም ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ጅምሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያካሄደው የመጅሊስ ምርጫ መንግስት በተለይም የሰላም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ጠይቀዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም መድረክ ላይ የሀገርን ስም ከፍ ለማድረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እየሰሩ ያሉትን ስራ ሚኒስተሩ አድንቀዋል።

May be an image of 4 people, dais and textበአፋርና በሱማሌ ወንድም ሕዝቦች መካከል የነበረውን የቆየ አለመግባባትና ግጭት ለመፍታት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሰራው ስራ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ ሁሉ አቀፍ የሰላምና የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የሃይማኖት ሀገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር እንደሌለባቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

May be an image of 10 people and textጠቅላይ ምክር ቤቱ አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት፣ እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ሀገራዊ የሰላም ጥሪና ዱዓ በጁምዓ ሰላት ላይ የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት ግጭቶች በንግግር እንዲፈቱ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ያቀረበ እና ለዚህም ቁርጠኝነቱ ያለው መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀው መጭው የመጅሊስ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

-----------