የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ 

ሰኔ 13/2016ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር )የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ጋር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ተልዕኮዎች ላይ ተቀናጅቶ  ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ 

የመግባቢያ ሰነድ  ስምምነቱ የሚዲያ ተቋማትን አቅም በመጠቀም ሀገራዊ የሰላም ግንባታና ብሄራዊ ተልዕኮዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል፡፡ 

ስምምነቱን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እንድሪስ  ተፈራርመዋል፡፡