“አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል ርዕስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር  24/2016 (አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታበሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲ ጋር በመተባበር የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

 ዶክተር ፋሪስ ደሊል የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት   በእንኳን ደህና መጣችሁ  ንግግራቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት  በአድዋ  ጦርነት   የተመዘገበው የጀግንነት ድል በመላው ዓለም ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች ታላቅ ኩራት ሆኖ ዛሬ ድረስ በትልቅ የድል ጀግነንነት እና ገድል የሚወሳ እና የሚዘከር የኢትዮጵያ የምንግዜም የአሸናፊነት ካዝማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል   የህብረ ብሄራዊ አንድነት ተምሳሌት   ለሀገር ህልውናና ክብር  ሲባል መስዋትነት የተከፈለበት  ዘላለማዊ ምልክት  መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

 

ዶክተር ፋሪስ አያይዘውም  የአድዋ ድል ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የድሉ ትሩፋት በልማት እና በሰላም አብሮ በመኖር ጭምር በተምሳሌትነት እንዲዘልቅና እንዲረጋገጥ፣ በአዲሱ ትውልድ ዘንድም ይህ የጋለ  የአንድነት ስሜት በተጨባጭ ሰርጾ፣ ከተገኘው ድል እና ጀግንነት በመማር ከዚህ ቀደም አባቶቻችን ውስጣዊ አንድነታቸውን አስጠብቀው የውጫዊ ወራሪ ሀይልን ሴራ ለመመከት መቻላቸውን በጥሩ ምሳሌነት በመውሰድ  እኛም  ከዚህ ትልቅ ተሞክሮ ወስደን ያሉብንን ውስጣዊ ችግሮች በግልጽ የምክክር መድረክ በመፍታት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ልማት እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ገልጸዋል፡፡  

በሰላም ሚኒስቴር የመንግስታት ግንኙነት ዴስክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ቸሩ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ መንግስትን መስርተውና ነጻነታቸውን አስከብረው ከኖሩ ቀደምት የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ መሆንዋን ገልጸው  ኢትዮጵያ ጥንታዊትና የራሷ የሆነ ረዘም ያለ የስርዓተ መንግስት ታሪክ ያላትና ይህንንም ከሞላ ጎደል ያስቀጠለች መሆኑን አስታውሰው  በአንጻሩ በተለያዩ ዘመናት ሀገሪቱን ያስተዳድሩት ስርዓተ መንግስታት የየራሳቸውን ትርክት ፈጥረው ይህንኑ ለማስረጽ መሞከራቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ እነዘህ ትርክቶች የሀገራችን ብዝሀነትን ያላማከሉ፣ የዜጎችን ፍላጎት እና መብት በማስከበር ላይ ያልተመሰረቱ በመሆናቸው ቅቡልነት ማግኘትና ህዝብን ለጋራ ዓላማ ማሰለፍ ባለመቻላቸው ለግጭትና አለመግባባት መንስዔ ሆነው መቆየታቸውን በመግለጽ  ሀገራዊ መግባባትን ለማጎልበት ሀገራዊ ማንነትን፣ እሴቶችንና ጥቅሞችን ለይቶ ማወቅና እንደዜጋ የጋራ ማድረግ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ለአብነትም አድዋ ሀገራዊ አንድነትና ጀግንነት በመምህር ታኑ ገትር ሀገራዊ ማንነት፣ ሀገረ መንግስትና ሀገረ ግንባታ ሀገራዊ ጥቅምና ተሞክሮ በመምህር በቃሉ ዋቺሶ እንዲሁም ሀገራዊ እሴቶች በመምህር አብዱልከሪም ሻፊ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች ቀርበው በቀረበው ጽሁፍ ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተነሱ በኋላ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

 ምንጭ፡- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ