ኢዜአ አሰባሳቢ ትርክትን ተደራሽ በማድረግ ለሀገር ግንባታ መሳካት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው - የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 24/2016(የሰላም ሚኒስቴር) ኢዜአ በኢትዮጵያውያን መካከል ብሔራዊ መግባባት የሚፈጥር አሰባሳቢ ትርክትን ተደራሽ በማድረግ ለሀገር ግንባታ ሂደት መሳካት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።

ተቋሙ ያለበት ቁመና አርበኝነትና የኢትዮጵያዊነትን ትርክት ለመገንባት እንደሚያግዘውም ተናግረዋል።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የኢዜአን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌከስ ጎብኝተዋል።

ኢዜአ ከቀደምት የኢትዮጵያ ተቋማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለረጅም ዓመታት የሀገሪቱ የመረጃ ማዕከል ሆኖ ስለማገልገሉ አውስተዋል።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ቀጣይነት ያለው የተቋማት ግንባታ ብዙ ፈተናዎችን ማሳለፉን ጠቅሰው፥ ኢዜአ 82 ዓመታት ራሱን አስቀጥሎ ዛሬ ላይ በተደራጀ ሁኔታ መገኘቱ ለብዙዎች ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል።

ለውጡን ተከትሎ መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ትኩረት መገናኛ ብዙሃን አስድናቂ ለውጥ እያመጡ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

ኢዜአ ባለፉት 5 ዓመታት ከነበረበት ችግር በመውጣት ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በማሟላት ከዘመኑ ጋር የሚመጥንና ተወዳዳሪ የዜና አገልግሎት መሆን የሚያስችለውን አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል።

የሀገርን አጀንዳ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ቴክኖሎጂ፣ መሰረተ ልማትና የሰው ሃይል ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢዜአ እነዚህን በማሟላት የሀገርን ገፅታ በዓለም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ዘላቂ የሰው ሃይል ግንባታ ላይ የጀመረው ለውጥም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ ለማድረግና ስሟን ለማስጠራት እንደሚያግዘው ጠቁመዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አክለውም ኢዜአ የተሰጠውን ብሔራዊ መግባባት የመፍጠር ተልዕኮ ዕውን ለማድረግ በተከታታይነት እየሰራ ስለመሆኑ የሰላም ሚኒስቴር ቀዳሚ ምስክር ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ያልተቋጨ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ ቀደም የነበሩ ትርክቶች የሀገረ መንግስት ግንባታው በተፈለገው መልኩ እንዳይሳካ ማድረጋቸውን አውስተዋል።

ትርክቶቹ ፍጹማዊ አንድነትና ፍጹማዊ ልዩነት ላይ ያተኮረ የነጠላ ፍላጎትን ብቻ የሚያስተጋቡ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

 ይህም በዜጎች መካከል ጥርጣሬ በመፍጠር የሀገር ግንባታ ሂደቱ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ገልጸዋል።

መንግስት ዜጎች ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጥሩና በሀገራቸው ላይ ወጥ የሆነ አቋም እንዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

 

በብሔራዊ ጥቅም፣ በሀገራዊ እሴቶች፣ በጋራ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ አንድ የሚያደርግ አዲስ ትርክት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በዚህ ረገድ ኢዜአ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ያለበት ቁመናም አሰባሳቢና ብሔራዊ መግባባት የተፈጠረበት የአርበኝነትና የኢትዮጵያዊነት ትርክት ለመገንባት እንደሚያግዘው ጠቅሰው፥ የሰላም ሚኒስቴርም ከኢዜአ ጋር አብሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

  ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብን በማቀንቀን ግንባር ቀደም ሀገር መሆኗን የገለጹት ሚኒስትሩ፥ ይህንን ሀሳብ በማስረፅ ረገድ እንደ ኢዜአ ያሉ ተቋማት ሚናቸው የላቀ ስለመሆኑ ተናገረዋል።

 ኢዜአ በትውልድ ቅብብሎሽ ሚናው የገዘፈ መሆኑን ገልፀው፥ አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት በነበሩበት ጊዜ ድምጻቸውን ሲያሰማ የነበረና የነጻነት ትግላቸውን በማቀጣጠልም ታሪክ የሚያነሳው ተቋም ነው ብለዋል።

 አፍሪካ በጨለማ ውስጥ የምትጓዝ አህጉር ተደርጋ የምትታይበትን የተዛባ ትርክት በማስተካከል ረገድም ኢዜአ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለበት ጠቅሰዋል።

 በተለይም የለውጡ መንግስት አንድነቷ የጠነከረና የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የጀመረውን ኢኒሼቲቭ ከዳር ለማድረስ ኢዜአ በአዲስ ምዕራፍ የጀመረው ጉዞ የሚደነቅ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ምንጭ፡-ኢዜአ