አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 18/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር)አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታበሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄ መርሐ-ግብ ተጀመሯል፡፡

 ንቅናቄው የአድዋ ድልን መታሰቢያ በማድረግ የኢትዮጵያ ወጣቶች ታሪካቸውን፣ ባህላቸውን እና እሴቶቻቸውን ተገንዝበው ለዘላቂ ሰላምና ሀገረ መንግስት ግንባታ መሠረት የሚሆን ሀገራዊ ንቅናቄ የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው፡፡

በንቅናቄው ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (/) ወጣቱ ግዙፍና ንቁ የኅብረተሰብ ክፍል እንደመሆኑ በሰላም እና ሀገር ግንባታ ላይ ወሳኝ ሚና ስላለው በተገቢው ሁኔታ አደራጅቶ ማሳተፍ ካልተቻለ ስኬታማ መሆን እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ የሰላም ግንባታ የእለት ተእለት ተግባርና ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እንደሚፈልግ በማስታወስ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በሀገራዊ አንድነት፣ ብዝኃነትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የተጀመረው የሰላም እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም አስተዳደራዊ መዋቅር ያሉ አካላት፣ ሚድያ፣ ሰላም ወዳዱ ሕዝብና ሁሉም የማኅበረሰብ አካላት ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት / ሙና አህመድ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግርኢትዮጵያዊያን በጋራ ሆነን ያቆምናቸው አሻራዎች የምንኮራባቸው፣ የምንጠራባቸው፣ የምንገለጽባቸውና የጋራ ስኬቶቻችን በአንድነት የመቆም ውጤቶች ናቸውና ዛሬም ለሁሉም ነገር መሠረት ለሆነው ሰላም በአንድነት ልንቆም ይገባልብለዋል፡፡

ግንባታ ሂደት ውስጥ ወጣቱ የሚኖረውን ሁሉን-አቀፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ በሰላም  ጉዳይ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትንና አብሮነትን ማጎልበት በትኩረት  ሊሠራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ሀገር አቀፍ የወጣቶች የንቅናቄ መርሐ-ግብሩን መጀመር አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች /ቤት የማኅበራዊ ልማት፣ የሰላምና ውጭ ጉዳይ፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፤ የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት ተወካዮች፤ የክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች /ርዕሳነ-መስተዳድሮችን፤ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊዎችን፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮችን፣ የወጣት ሊግ አመራሮችን ያሳተፈው የውይይት መድረክ በሰላም ሚኒስቴር እና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡