የፕሮጀክት ስምምነት ተደረገ
የፕሮጀክት ስምምነት ተደረገ
የፕሮጀክት ስምምነት ተደረገ
ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር Empathy for Life Integrated Development Association – (ELIDA) ጋር በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
Empathy for Life Integrated Development Association – (ELIDA) ከዚህ ቀደም ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ዘርፈ ብዙ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ተቀናጅቶ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ በጋራ እየሠራ ያለ ድርጅት መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አወቀ አጥናፉ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መሪ ሥራ አስፈፃሚው አወቀ አጥናፉ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ በዛሬው ዕለት የተደረገውን የፕሮጀክት ስምምነት አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ በተለይም በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም እና የጥላቻ ንግግሮች ላይ አተኩሮ በመሥራት ግጭት ቀስቃሽ እንቅቃሴዎችን በመከላከል የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ለማጎልበት ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ !