በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቦንጋ ከተማ ለዞን እና ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቦንጋ ከተማ ለዞን እና ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
የሰላም ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ሥርዓት፣ በግጭት መረጃ አሰባሰብ፣ ሪፖርት አቀራረብ እና በግጭት አስተዳደር ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ፣ የግጭት አመላካች መረጃዎች አሰባሰብንና ትንትና ስልቶችን፣ የግጭት ታሪካዊ ዳራንና እውነትኛ መንሥዔ መለየትን፣ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዐቶች ግጭትን ለማስተዳደር ያላቸውን ፋይዳ፣ እንዲሁም የግጭትን ተለዋዋጭ ባህሪያትን በመረዳት ግጭትን ማስተዳደር፣የሁኔታ መከታተያ ክፍል ውስጣዊ አደረጃጀት እና የግጭት አመላካች ክስተትና ሁኔታን በተመለከተ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ የተሰራበት መሆኑ ተገልጿል።
ሰልጣኞች በየአካባቢያቸው ማህበረሰቡ የሚጠቀምባቸውን የግጭት አመላካቾች ካላቸው ልምድ ጋር በማጣመር ሀሳብ የተለዋወጡበትና ዘላቂ ሰላምን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን ያገኙበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ስለመረጃ አሰባሰብ፣ በማን ምን፣ እንዴት፣ መቼ የሚሉ የመርጃ እሰባሰብ ሂደቶችንና የመረጃ ምንጮች ስለመለየት ያላችውን ግንዛቤ አካፍለዋል።
የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መዋቅራዊ ችግሮች በሂደት እየተፈቱ የሚሄዱ በመሆናቸው በተቀመጥንበት ቦታ የመፍትሄ ሰዎች መሆን እንደሚያስፈልግና ለዚያ አራስን ማዘጋጀትና ማብቃት እንዲሁም በያዛችሁት እውቀት ላይ ጨምራችሁ ታች የቀሩትን የማብቃት ሥራ ሰርታችሁ ተደጋግፈን የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳት ያስፈልጋል በማለት የስልጠናው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አለሙ ስልጠናው የነበረንን እንድናዳብር ፣ ያልሰራናቸውንና የረሳናቸውን እንድንሰራ፣ በአሰራር ሥርዐት ላይ የነበሩ ማነቆዎችን እንድንፈታ፣ የግጭት ቀጠናዎችን በትኩረት በመለየት ትክክለኛ መረጃን ከትክክለኛው ምንጭ በመቀበል ወቅታዊነታዊነታቸው ተጠብቆ ከመተንተን አንጻር ያለብንን ክፍተት የሚሞላ በመሆኑ ሰልጣኞች ያገኛችሁትን እውቀት እስከታች እንዲደርስ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። አቶ ሃብታሙ አክለውም የሰላም ሚኒስቴር ይህን ስልጠና በዚህ መልክ ተገናኝተን እንድንሰለጥን ጎደሎውን እና ጥሩውን ለይተን እንድናይ የማንተዋወቅ እንድንተዋወቅ፣ እንደ ክልል በአንድ ዘርፍ ለምንሰራ አንድነት እና ወንድማማችነት እንዲኖረን የራሱ አስተዋጸኦ ያለው ስልጠና መሆኑን ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሰላም ለኢትዮጵያ!