የ2017 በጀት ዓመት የአምስት ወራት ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ግምገማና የሥራ ትውውቅ ተካሄደ
የ2017 በጀት ዓመት የአምስት ወራት ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ግምገማና የሥራ ትውውቅ ተካሄደ
ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ አማካሪዎችና መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት አምስት ወራት በየዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና የሥራ ትውውቅ አካሂደዋል።
በውይይቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት፣ የታዩ ውስንነቶችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የውይይቱ ዋነኛ አላማ በምናደርገው የሥራ ትውውቅ ተመሳሳይ ግንዛቤ ለመያዝና ለመደጋገፍ መደላድል መፍጠር በመሆኑ በተቋሙ ባለፉት አምስት ወራት በሰላም ግንባታ፣ በሀገር ግንባታ፣ በብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ በፌዴራሊዝምና መንግሥታት ግንኙነት እንዲሁም በግጭት አስተዳደር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል።
እንደ ሀገር የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል፣ ዘላቂ ሰላም ለመገንባትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሁሉም በየተሰማራበት መስክ መረባረብ ይገባል ያሉ ሲሆን ከተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር አሁን ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል።