የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
ዛሬ ታህሳስ 04 ቅን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑትን አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ከመገንባት ፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ከመመለስ ፣ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ከመስጠት እና ብሔራዊ መግባባትን ከመፍጠር የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በሰፊው አብራርተዋል ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላም ከመገንባት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን ከተቋማቸው ተልዕኮ ጋር የሚናበብ መሆኑን መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት በግጭት መከላከል እና በሰላም ግንባታ ስራዎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።