“ኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ የሄደችባቸው መንገዶች” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተደርጓል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ “ኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ የሄደችባቸው መንገዶች” በሚል መሪ ርዕስ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

በፓናል ውይይቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ስትራቴጂ ፣ የምክክር ኮሚሽኑ ዕድሎች እና ፈተናዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

May be an image of 2 people, table and daisየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አካያ ያጋጠሙ ችግሮች እና ችግሩን ለመፍታት የተከናወኑ ተግባረትን በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡

May be an image of studyingየኢትዮጵያ የአረንጋዴ ልማት ስትራቴጂ እና የአካባቢ ጥበቃን ከማረጋገጥ አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር ያስቀመጡት ደግሞ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አስፋው (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ከላይ በቀረቡ ሃሳቦች ላይ ከተሳታፊዎች ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡