በአህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መልእክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሰላም ሚኒስቴር አህጉራዊ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡ ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኮንፈረንሱ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው “የፕሪቶሪያው ስምምነት ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን ችግር በአፍሪካዊያን መፈታት አለበት የሚለውን አቋም በጽኑ እንደምታምን በተግባር ያሳየ ነው” ብለዋል፡፡

ክቡር ፕሬዚዳንቱ አህጉራዊ አጋርነት እና በአፍሪካ የሀገራት ትብብር ለሰላምና ዕድት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን አንስተው ግንኙነቶችን በማጎልበት የበለጠ የተቀናጀ፣ ጠንካራ እና የበለፀገ አህጉር ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች መጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡No photo description available.

May be an image of one or more people, dais and text"የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ ቀጣናዊ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር እንዲፈጠርና እንዲስፋፋ የሚያደርግ፤ ብሎም ለፖሊሲ ጥናቶች ገንቢ ሚና ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡