የሰላም ሚኒስቴር አህጉር አቀፍ የሰላም ጉባዔ ሊካሄድ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 13/2017 . (የሰላም ሚኒስቴር)- የሰላም ሚኒስቴር አህጉር አቀፍ የሰላም ጉባዔ ሊካሄድ ነው፡፡

የሚካሄደው አህጉራዊ የሰላም ጉባዔ በአፍሪካ አህጉር ሰላምና ብልጽግናን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ወሳኝ እና መሪ ሐሳቦች ላይ ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተመላክቷል

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (/) አህጉር አቀፍ የሰላም ጉባዔውን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውምኢትዮጵያ በአህጉር ደረጃም ሆነ በዓለም ደረጃ ሰላምን በማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራት ሀገር ነች፡፡ ለአፍሪካ ነፃነት፣ ሰላም እና መልካም አስተዳደር እጅግ ብዙ ያበረከተች ሀገር ናት፡፡ አሁን ባለንበት ወቅታዊ ሁኔታም ቢሆን በቅርቡ የምናያቸውን ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ ፈተናዎች በመቋቋም የሰላም ግንባታ ሥራዎችን አጠናክራ እየመራች ያለች ሀገር ነች፡፡ የኢትዮጵያን የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ልምድ በማካፈል፣ በአፍሪካ ሀገራት መረጋጋት እና እድገት ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ያሉትን የሰላም ችግሮች በመፍታት አህጉራዊ ሰላምና ብልፅግና እንዲረጋገጥ ለማድረግ የተዘጋጀ አህጉራዊ ጉባዔ ነው ብለዋል

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡት መግለጫበአፍሪካ ሀገራት መካከል ትብብርን እና አንድነትን በማጠናከር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን፣ አህጉራዊ ትስስርን እና የጋራ ዓላማዎችን የሚያጎለብት ብዝኃነትን እንደ ጥንካሬ ምንጭ ለመጠቀም የበለጠ የተቀናጀ፣ ጠንካራ እና የበለጸገች አህጉር ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ከፍ የሚያድግ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አፍሪካዊያን በውይይት የጋራ ጥረቶችን በማጣመር እና በመተባበር አፍሪካ 2063 (እአአ) ለማሳካት ያስቀመጠችውን የሰላም ግብ ማሳኪያ አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ጉባዔ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ጉባዔው የሚካሄደው ኅዳር 16-17/2017 . በአዲስ አበባ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል መሆኑን እና የአፍሪካ መዲና በሆነችው ከተማ እየተከናወኑ ያሉት አንዳንድ የልማት ሥራዎችም ጉብኝት የሚደረግ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡