የሰላም ሚኒስቴር የ10 ወራት ዋና ዋና አፈፃፀም እና ቀጣይ የትኩረት አቅጫጫዎች አስመልክቶ ከሰራተኞች ጋር  ውይይት አካሂዷል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ የ11 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር የ10 ወራት ዋና ዋና አፈፃፀም እና ቀጣይ የትኩረት አቅጫጫዎች አስመልክቶ ከሰራተኞች ጋር  ውይይት አካሂዷል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ አቶ ብናልፍ አንዱአለም የዛሬው መድረክ ዓላማ እንደ ሀገር(at Macro levl) ያለንበትን ሁኔታ ማየት  እና የሰላም ሚኒስቴር ከተሰጠው  ዋና ተልዕኮ አንፃር ምን ላይ ነው ያለነው  የሚለውን ለማየት ነው ብለዋል።

''የሰላም ሚኒስቴር የ10 ወራት ዋና ዋና አፈፃፀም  ሪፖርት እና ቀጣይ የትኩረት አቅጫጫዎች''  በሚል ፅሁፍ ያቀረቡት የሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ አዱኛ በቀለ ተቋሙ  በሰላም ግንባታ ፣በሀገር ግንባታ፣ በሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በግጭት  አስተዳደ ፣በፌዴራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት ላይ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት አቅርበዋል።

በቀረበው ሪፖርት እና አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ከሰራተኞች  ሃሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።