የ10ኛ ዙር  የሰላም  በጎ ፈቃደኞች ተመረቁ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 8/2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከሐዋሳ  ዩኒቨርስቲ  ጋር በመተባበር በ10ኛው ዙር መርሐ ግብር  ያሰለጠናቸውን የሰላም በጎ  ፈቃደኛ ወጣቶች በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ዛሬ አስመርቋል።

የምረቃ  ስነ ስርዓቱ በሐይማኖት አባቶችና በሐገር ሽማግሌዎች  ምርቃት ተጀምሯል። 

 

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ

 "በጎነት ለአብሮነት በሚል መሪ ሐሳብ በሰላም ሚኒስቴር የተጀመረው  የሰላም የወጣቶች በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም  ዓላማ የወጣቱን አመለካከት፣ ክህሎትና ሞራል በመገንባት እንዲሁም አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት እንዲያውቅ በማድረግ ፤ በማንነቶች ላይ መሠረት አድርጎ ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ  መግባባት ማረጋገጥ  መሆኑን ተናግረዋል። 

የሰላም ሚኒስቴር አወንታዊ ሰላም ከሚገነባባቸው  መንገዶች መካከል አንዱ የሰላም የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ነው ያሉት አምባሳደር እሸቱ ደሴ  በዚህ ፕሮግራም የሰላም አምባሳደሮች ተፈጥረዋል፣ህዝቦች ተቀራርበዋል፣ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ዳብረዋል፣ ብዝሃነትን እንደ በጎ እድል የመቆጠር ሃሳብ አድጓል፣ በጎ የመስራት ሃሳብ ጎልብቷል፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ስሜት ከፍ ብሏል  ብለዋል።

በጎ ለመስራት የአካል፣ የስነ ልቦና እና የአይምሮ ዝግጁነት ብቻ ነው የሚጠይቀው ያሉት አምባሳደሩ  ዛሬ የተመረቃችሁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተጣለባችሁ ሃላፊነት ትልቅ መሆኑን ተረድታችሁ በሄዳቹሁበት ሁሉ ኢትዮጵያውያነትን እንድትሰብኩ አደራ እላለሁ ብለዋል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር  አያኖ በራሶ በበኩላቸው  ኢትዮጵያ የሰላም፣የብዝሃነት፣የአንድነት እና የእኩልነት ሀገር ሆና እንድትቀጠል የበጎ ፈቃድ ስራ በእጁጉ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን  ዛሬ የተመረቃችሁ የሰላም  በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች  ለዩኒቨርስቲያችን ውበትና ኩራት ነበራችሁ፤ በሄዳቹሁበት ሁሉ የሰላም አምባሳደር ሁናችሁ እንድታገለግሉ ጥሪ አስተላልፋለሁ ብለዋል።

በ10ኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሲሰለጥኑ የቆዩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከስልጣናቸው ጎን ለጎን  የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸው ተገልጿል።
 
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ  አመራሮች ፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ተወካዮች ፣ የሐገር ሽማግሌዎና  ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከ 2013 ዓ.ም ጀምሮ  ለ10 ተከታታይ ዙር ባካሄደው የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ከ48 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን አሰልጥኖ በተለያዩ የሀገራችን ክፍል  አሰማርቷል፤እያሰማራም ይገኛል።