የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ሮበርት ፒፐር ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ዛሬ ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ከሆኑት ሮበርት ፒፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በውይይቱ የሰላም ሚኒስቴር በግጭት ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመጠለያ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ወደቀያቸው ለመለስ ያለውን ሂደት አብራርተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስቴር ደኤታው አያይዘውም በመልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የጋራ እቅድ በማውጣትና በጀት በመመደብ በቅንጅት ስራው እየተሰራ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ የሆኑት ሮበርት ፒፐር በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴር በመልሶ ማቋቋም ሂደት ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው አስፈላጊውን የበጀት ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ፈቃደኝነት ገልፀዋል፡፡