የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ መሰረቱን ዩናይትድ ኪንግደም ካደረገው ኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ መሰረቱን ዩናይትድ ኪንግደም ካደረገው ኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ መሰረቱን ዩናይትድ ኪንግደም ካደረገው ኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በውይይቱ ለተገኙ የኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ሃላፊዎች የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ አክለውም የሰላም ሚኒስቴር የዘላቂ ሰላም ስራዎችን እና የብሔራዊ መግባባት ተግባራትን ለማጎልበት በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይትም የዚህ አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡
የኦክስፎርድ ፖሊሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ሪች ዊሊያምስ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በቀጣይ ከተቋሙ ጋር በተለያዩ የማማከር ስራዎች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡