በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት አስተዳደራዊ አዋሳኝ አካባቢዎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 8/2016 ዓ፣ም (የሰላም ሚኒስቴር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና በአሮሚያ ክልል መንግስት አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ለመምከርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ከሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ፣ከዞንና ወረዳ አሰተዳዳሪዎችና ከፀጥታ መዋቅር አመራሮች ጋር ምክክር ተካሄዷል፡፡

 

 የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ሰላም ከራስ ይጀምራል ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፤ የፀጥታ ጉዳይ ድንበር የሌለው በመሆኑም በቅንጅት ሁላችንም ለሰላም ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት በተናጠል የምንሰራቸው ስራዎች እንዳሉ ሆኖ ዛሬ የምናካሄደው ምክክር በመደጋገፍና በተቀናጀ መልኩ የአካባቢያችንና የማህበረሰቡን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት  የሚያስችል መድረክ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

 የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የሰላም እሴት ግንባታና የግጭት መከላከልና አፈታት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሃይሌ ጉርሜሳ የዚህ መድረኩ ዓላማ የመሰረተ ልማት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና አብሮነትን በማጠናከር   አስተማማኝ ሰላም ማስፈን   ነው ብለዋል።

የመንግስታት ግንኙነት በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት በሚል ርዕስ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በሰላም ሚኒስቴር የመንግስታት ግንኙነት ዴስክ ኃላፊ በሆኑት አቶ ግርማ ቸሩ ቀርቧል ፡፡

በሁለቱም ክልሎች የመንግስታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በተመለከተየህዝቦች አብሮነት ያለበት ደረጃ መልካም የሚባል እና በአጎራባች ቀበሌዎች አካባቢ ጎልቶ የሚታይ የፀጥታ ችግር  እንደሌለ ተመላክቷል፡፡