ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን ተሰርተው የተጠናቀቁ ቤቶች ርክክብ ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 4/2016 . (ሰላም ሚኒስቴር ) የሰላም ሚኒስቴር ከአሶሳ ከተማ ከተማ አስተዳደርና  ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  ጋር በመተባበር በክረምቱ የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር በአሶሳ ከተማ  ግንባታ ያስጀመራቸውን ቤቶች አጠናቆ  ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን አስረክቧል።

በርክክብ ፕሮግሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር  የሚኒስትር /ቤት ኃላፊ  / ሂሩት ዲሌቦ  የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ የተለያዩ ሀገራዊ እና ህዝባዊ ጥሪ በመቀበል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ይህ የበጎ አድራጎት ተግባርም የዚህ  አንድ አካል ነው ብለዋል  

 

/ ሂሩት አክለውም  የሰላም ሚኒስቴር አወንታዊ ሰላም እንዲጎለብት እና በህብረተሰቡ ዘንድ የሰላም ፅንስ ሃሳብ ሰርፆ እንዲገባ እየሰራ  እንደሚገኝ ገልፀው ኢትዮጵያውያን ዕርስ በዕርስ ከተረዳዳን የማንወጣው ችግር የለም ብለዋል።

 

ይህ የበጎ  አድራጎት ተግባር  ሰው ተኮር ፕሮግራም ነው ያሉት / ሂሩት እኛ የሰጠነው መነሻ ነገር ነው፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደርና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፕሮጀክቱ ዳር እንዲደርስ በማድረጋቸው አመስግነዋል።

የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱከሪም አብዱራሂም እና የቤንሻንጉል ክልል የሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኋላፊ አቶ  አብዱሰላም  አብዱራሂም  በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴር ላደረገው ድጋፍ እና የህዝብ አለኝታነት አመስግነዋል።

ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ 5 ቤቶች ተሰርተው  ርክክብ የተደረገ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር ለቤት ግንባታው  1.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን  የአልባሳትና የመኝታ ፍራሽም ድጋፍ አድርጓል።

 ቤት የተረከቡ  ኑዋሪዎች  የሰላም ሚኒስቴርን፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደርና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ላደረገላቸው  ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።