ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በኢትዮጵያ የዩኤስአይዲ (USAID), ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን ስኮት ሆክላንደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ዛሬ ኅዳር  26/2016 . የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በኢትዮጵያ የዩኤስአይዲ (USAID), ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን ስኮት ሆክላንደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም  በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን  ወደ ቀድሞ ቀያቸው ለመመለስና ለማቋቋም በጋራ ስለሚሰሩበት መንገድ እና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን በሰላም ትጥቅ ፈተው ከህብረተሰቡ ጋር ለመቀላቀል የሚደረገውን ሂደት ስለሚደግፉበት ሁኔታ ተወያይተዋል።

 ከዚህ በተጨማሪ የምክክር  ሂደቱ  ውጤታማ ሰለሚሆንበት  መንገድ ተወያይተዋል።