የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል "ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት "በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ከወራቤ ዩኒቨርሲ ጋር በመተባበር "ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት " በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት መምህርት አለዊያ ሀሰን መድረኩ ለብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር እንዲሁም ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት የተለያዩ ምሁራን ተወያይተው በሀገር ደረጃ የተጠናከረ ሀሳብ የምናገኝበት እና የምናዳብርበት የውይይት መድረክ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ባለድርሻ አካል ግብዓት የሚሆን ሀሳብ በማመንጨት በኩል የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል ።May be an image of 1 person, dais and text

May be an image of 1 person and beardየውይይት ሰነዱ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር መሀመድ ድሉ የብሔራዊ ጥቅም በምሁራን እይታ ምን ይመስላል? ለአንድ ሉዓላዊ አገር ከሚጠቅሙ አለም አቀፋዊ ጥቅሞች አንፃር እና የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ ምን ይመስላል? የሚሉ እና ሌሎች መሰል መነሻ ሀሳቦች በዝርዝር ቀርበዋል ውይይት ተደርጎበታል።May be an image of 1 person, headscarf, dais, newsroom and text

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎችም ለሰነዱ ግብዓት የሚሆኑ በርካታ ገንቢ ሃሳቦችን አንስተዋል።