በሀዋሳ ከተማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሲዳማ ክልል የሰላምና ፀጥታ መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎችን በፌዴራሊዝም፣ በግጭት አስተዳደር እና በመንግሥታት ግንኙነት ፅንሰ-ሐሳብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ለሲዳማ ክልል የዞን እና ወረዳ አመራሮች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

 ስልጠናው የማስፈጸም አቅም በመገንባት በሰላም ግንባታው የአመራሩን ሚና ተሳታፊ ለማድረግ ያለመ ስልጠና ነው፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የግጭት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይርጋለም መንግሥቱ ግጭቶችን ለማስወገድ፣ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን፣ ግጭቶች ሲከሰቱ የሚፈጠሩ ጉዳቶችን ለመቀነስ በቅንጅት ከመሥራት አንጻር ክፍተት መኖሩን በመግለጽ፤ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ለመቆጣጠር እንዲቻል የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ አሰፋ እንደገለጹት ግጭት ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ በክልሉ ለበርካቶች ሞትና ስደት ምክንያት ሲሆን እንደቆየ በማስታወስ አሁን ግን ክልሉ በሰላም ወዳዱ ሕዝብ የጋራ ጥረት መረጋጋትን ማስፈን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

 

በስልጠናው የተገኙ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ አመራሮች፣ የሰላምና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች የተረጋጋ ሰላም ለማስፈን ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት እና የየአከባቢዎችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የትብብር አሠራር መከተል እንደሚገባ በውይይቱ አንስተዋል። የሰላም ጠንቅ የሆኑ ጉዳዮችን ማጥራትና የሕግ ማስከበር ተግባራትን በቁርጠኝነት ማከናወን ያስፈልጋልም ብለዋል። በተጨማሪም የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች በክልሉ ሰላም ለማምጣት የተደረጉ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በርግጥም ውጤት ያመጡ ቢሆንም ከችግሩ ውስብስብነት አንፃር የሁሉንም ትጋትና ጥረት የሚጠይቁ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው በግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ፣ በግጭት አስተዳደርና ዘላቂ መፍትሔ ላይ ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት የጋራ ግንዛቤ ማዳበር የተቻለበት መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡