የ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርምና ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ
የ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርምና ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርምና ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ በየዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርምና የማክሮ ኢኮኖሚ በየዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ ተወካይ በአቶ አዱኛ በቀለ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) መንግስት በዋነኝነት አወንታዊ ሰላም ላይ በጀት በመመደብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደሀገርም የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል፣ የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ለውጡን ለማፅናት ሁሉም በተሰማራበት መስክ መረባረብ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።