የሰላም ሚኒስቴር ከአሜሪካ ፍሬንድስ ሰርቪስ ኮሚቴ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ከአሜሪካ ፍሬንድስ ሰርቪስ ኮሚቴ (American Friends Service Committee – FSC) ጋር በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሥራ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰንድ ተፈራርሟል፡፡May be an image of 4 people and dais

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በፊርማው ሥነ-ስርዓት ባሰሙት ንግግር በማኅበረሰብ ውስጥ ያሉትን የሰላም ግንባታ እና የግጭት አፈታት እሴቶችን በማጎልበት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉትን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ውጤታማነቱን ከፍ ለማድረግ በትብብር መሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰንድ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የተደረገው ስምምነት የተቋማት አጋርነትን እና የትብብር ሥራ የሚፈልጉ የጋራ የሆኑ የሰላም ዓላማዎችን እንዲያሳኩ ፤ የታቀዱ ተግባራትን በተሟላ መንገድ ለማከናወንና በጋራ ጥረት የሚያመጡ አዎንታዊ ውጤቶችን ለማሳደግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !