በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ሕዝብ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከሩሲያ አምባሳደር ኤቭጄኒ ተርክሂን ጋር ውይይት ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ሕዝብ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጄኒ ተርክሂን ገለጹ

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ጋር በሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ አብረው መሥራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ውይይት አድረገዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ኢትዮጵያና ሩሲያ የረጅም ጊዜ የታሪክ እና የባሕል ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው በየትኛውም የፈተና ጊዜ ተጠብቆ የቆየው የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ኢትዮጵያ ለምታደርጋቸው ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሚያከናውናቸው የሰላም ግንባታ ሥራዎች የሩሲያ ድጋፍና አጋርነት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጄኒ ተርክሂን በበኩላቸው ሩሲያ ለኢትዮጵያ ሁል ጊዜም አጋር መሆኗን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ለምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሀገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ታሪካዊ ግንኙነት መጠናከር ለሚያከናውናቸው ተግባራት ተገቢ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡