በአፋርና ሱማሌ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን ለመፍታት ውይይት እና የመስክ ምልከታ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር በአፋርና ሱማሌ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራትን እና በቀጣይ ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራትን አስመልክቶ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ውይይትና የመስክ ምልከታ አከናውኗል።

በአፋርና በሱማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ የተሰሩ ስራዎችን እና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ ጉዳዮች አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡት በሚኒስትር ዴዔታ ማዕረግ የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ የሰላም ሚኒስቴር፣የፌዴራል ፀጥታ ተቋማት፣የአፋርና የሱማሌ ክልሎች በሰሩት ከፍተኛ የቅንጅት ስራ በሁለቱም አዋሳኝ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም መታየቱን ገልፀዋል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም በግጭት ውስጥ የነበሩ እና ወደ ሰላማዊ ቀጠና የተመለሱ አካባቢዎችን የተመለከቱ ሲሆን ተኩስ እንዲቆምና ግጭቱ እንዲረግብ መደረጉ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በቀጣይ ዜጎችን በዘላቂነት ማቋቋምና ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ስራ ይከናወናል ብላዋል።

ግጭቱን ለመፍታት ሁለቱ ክልሎች የወሰዱት ቁርጠኝነት መልካም ነበር ያሉት ክቡር አቶ ብናልፍ የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት የሰሩት የሰላም ስራም የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ተግባራትን ማጠናቀቅ እና ለግጭት መነሻ የሆኑ የወሰን ጉዳዮችን መፍትሄ መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ የአፋርና ሱማሌ አጎራባች አካባቢዎች በተደረገው የመስክ ምልከታ ፕሮግራም ላይ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች፣የፌዴራል ተቋማት የፀጥታ አመራሮች፣የአፋር ክልል የፀጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።