የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ.ር) ስምምነቱ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉትን የአዎንታዊ ሰላም ግንባታ ሥራዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ወደ ብዙኃኑ ሕዝብ ለማድረስ የተደረገውን ትኩረት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የሀገር ግንባታ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ የተቋማት ቅንጅትና ትብብር በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አክለው ለሰላምና ሀገራዊ አንድነት የጋራ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ባስተላለፉት መልዕክት አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ መሳፍንት ተፈራ “የሀገር ግንባታ ሥራውን በዜጎች ጭንቅላት ለማስረጽ አንዱ መሣሪያ የተግባቦት ሥራ (ኮሙኒኬሽን) ስለሆነ ሥራውን በቅንጅት አጠናክሮ ለመሥራት ስምምነቱ ፋይዳው ከፍተኛ ነው” ብለዋል፡፡
በሀገር ግንባታ የሚሠሩ ሥራዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚያስችሉ እና በኮሙኒኬሽን ሥራዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት የአቅም ግንባታ ሥራዎች በስፋት እንደሚሠሩ ተጠቁሟል፡፡