ኢትዮጵያዊ በጎ እሴቶችና ዓለም አቀፋዊነት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሀገራችን በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ ለረጅም ዘመናት ተገንብተው የኖሩ እጅግ አስደናቂ የሆኑ መልካም እሴቶች ብዙ አሉን፡፡ እነዚህ ማህበራዊ እሴቶቻችን በትውልድ ተግንብተውና ተጠብቀው የመጡ እንደመሆናቸው ለተተኪ ትውልድ ቢተላለፉ በሀገራችን ላይ የተረጋጋ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከማድረግ አንጻር የጎላ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፡፡

በሀገራችን በሁሉም ማኅበረሰቦች ውስጥ ያሉ የአብሮነት፣ የትብብር፣ የመረዳዳት፣ የመተጋገዝ፣ የመደጋገፍ እና ማኅበራዊ ችግሮች በጋራ የሚፈቱበት እንዲሁም የእርቅ ሥርዓቶች የሚፈፀሙበት እና አለመግባበቶችን በውይይት የመፍታት ነባር እሴቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ያደጉ የበለፀጉ እና ቀና ብለን እንድንቆም የሚያደርገን የነጻነት ታሪካችንም መሠረት የሆኑ ናቸው፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው ዓለም አቀፋዊነት (Globalization) ኢትዮጵያዊ የሆኑ መልካም እሴቶች እንዳይሸረሸሩ መጠበቅ፣ መንከባከብና ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ የማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን የመወጣት የሞራል ግዴታ አለብን፡፡

ሰላም ለኢተዮጵያ !