የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስቲያናት ፅ/ቤት አመራሮች ጋር ትውውቅ አደረጉ
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስቲያናት ፅ/ቤት አመራሮች ጋር ትውውቅ አደረጉ
ዛሬ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስቲያናት ጽ/ቤት አመራሮች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ሃይማኖት ማለት ሰላም ማለት በመሆኑ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከርና ጥላቻን በማስወገድ የሚያጋጥሙንን ማህበራዊ ችግሮች በመቅረፍ በጋራ በመሆን የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ያለመ የትውውቅ ፕሮግራም እንደሆነ ገልፀዋል።
ክቡር አቶ መሐመድ አክለውም ሀገራችን ብዙ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ያሉባት እንደመሆኗ ግጭቶች ሊስተዋሉ አይገባም፤ በአብሮነት ለሰላም መስራት ይገባል፤ የሰላም ሚኒስቴርም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት አብያተ ክርስቲያናት ሰላም ለማስረፅ ለምታደርገው ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያናት የጳጳሳት ጉባኤ ኘሬዝዳንትና የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ደ. ሱራፌል በበኩላቸው በፊት የነበረንን መከባበርና መቻቻል ማምጣት እንዲቻል የሃይማኖት ተቋማትም ሆነ መንግስት ስነ-ምግባርን የማስረፅ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በሀገራችን ሰላም ጉዳይ እንደከዚህ ቀደሙ በጋራ ለመስራ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል ።