ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር ) ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃል በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚቆይ የልሂቃን ውይይት የንቅናቄ መድረክ ተጀመረ።

የቀጠናውን ትስስር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በማይነካ መልኩ ማዳበር እንዲቻል ትኩረት በሚደረግባቸው ነጥቦች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ሀገራችን ኢትዮጵያ ለቀጠናዊና ለአህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት ስትሰራ የነበረችና ዛሬም እየሰራችም ያለች መሆኗን ገልፀው ቀጠናውን ማስተሳሰር የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም በሚያረጋግጥ መንገድና ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ መልኩ በመንግስት በልዩ ትኩረት እየተመራ ነው ብለዋል። ለዚህ ስኬት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚኒስቴር መ/ቤታችን ጋር ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የልሂቃን ውይይት በማዘጋጀት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው የዘንድሮው የንቅናቄ መድረክም በተሳካ ሁኔታ እንደሚካሄድም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

May be an image of 1 person, studying, dais and newsroomጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ሮባ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና እና ለዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ እንደመሆኗ መጠን የቀጠናውን ትስስር ለማዳበር እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የምጣኔ ሀብት እድገትን የሚያፋጥኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ማውጣት እና መተግበር፣ ወዳጅ እና አጋር ሀገራትን ማብዛት ፣ በመርህ ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የደህንነት ተቋማት ብቃትን ማሳደግ፣ ብሔራዊ ጥቅምን የሚገዳደሩ ሁኔታዎችን በዓለም አደባባይ መሞገት እንደሚገባ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ጠቅሰዋል፡፡

May be an image of 2 people and daisበኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት መካከል ያለው ድንበር ዘለል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችና አብሮነት፣ እንዲሁም በቋንቋና ባህል የዳበረ ትስስርን በመጠቀም በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ቀጠናዊ ትስስርን ማዳበር ለቀጠናችን ሰላምና ደህንነት ድጋፍ አስተዋፅኦ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡በንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረኩ የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ፎካል ፐርሰኖችና የክልልና ከተማ አስተዳደሮች የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።