የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በተቋሙ ተግባርና ተልዕኮ እና ቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በተቋሙ ተግባርና ተልዕኮ እና ቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።

May be an image of 1 person, newsroom and daisክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የዛሬው ውይይት ተቋማችን እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ለማጠናከር እና የተሰጠንን ሀገራዊ ኃላፊነት በላቀ ሁኔታ ለመወጣት ያለመ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ሰው ተኮር የሆነ አሰራር እንከተላለል ያሉት ክቡር አቶ መሀመድ በቴክኖሎጅ የተደገፉ ስርዓቶችን በመዘርጋት ተቋሙን ውጤታማ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

May be an image of studying and crowdሀገራችን የምንሰጣትን ነው የምትሰጠን ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ያለንን ዕውቀት፣ ጊዜና ሀብት ያለ ስስት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ልናበረክት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ አክለውም ተቋማዊ አሰራር ግልፅ እና ተጠያቂነት ሊኖራቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ህሊናን፣ መረጃን እና ህግን መሰረት ያደረጉ አሰራሮችን ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል ።

በውይይቱ ላይ ሊስተካከሉ እና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሰራተኞች ሃሳባቸውን አንስተዋል።