የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት የስልጠና እና የስምሪት አፈጻጸም፤ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ እና ፕሮግራሙ ባስገኛቸው ውጤቶች ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል፡፡

የውይይቱ ዓላማ ፕሮግራሙ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በማጥናት የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና የባለ ድርሻ አካላትን ሚና ያቀናጀ ቀጣይነት ለማጠናከር ነው፡፡

May be an image of 7 people and daisየሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት “የበጎ ፈቃድ ተግባር ብዙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ያሉት ስለሆነ በስፋት ሊሠራ የሚገባ እና እንደ ሀገርም ባህል ሆኖ መቀጠል ያለበት ነው”፤ ብለዋል፡፡ ፕሮግራሙ የሚያስገኘውን ሀገራዊ ጥቅሞች በማብራራት “የሀገራችንን ማኅበራዊ ችግሮች የምንፈታበት አንዱ መንገድ ሰው በራሱ ፈቅዶ በሚሠራ ሥራ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

ሀገራዊ ፕሮግራሙ በጥናቱ የተዳሰሱ ቦታዎች ላይ ያመጣውን ውጤት እና የታዩ ክፍተቶችን በጥልቀት በመመልከት ይበልጥ ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላቱ በየደረጃቸው ስልቶችንና አሠራሮችን በጋራ ተቀናጅተው መቀየስ እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

May be an image of 3 people, dais and text

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ያለው የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም በሀገር ግንባታ ላይ መንግሥት እየወሰደ ባለው ቁርጠኛ አቋም አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አመላክተው፤ ፕሮግራሙ በላቀ ደረጃ እየጎለበተ እንዲሄድ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡May be an image of 2 people, dais and textMay be an image of 2 people and text

May be an image of 2 people, dais and textMay be an image of 2 people, dais and text

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ውይይቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሀገራዊ አንድነትና ለዘላቂ ሰላም እንዲሁም ያደገችና የበለፀገች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ተገቢውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ባለድርሻ አካላቱ ተቀናጅተው በጋራ እንዲሠሩ የሚያደረግ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ስለ ፕሮግራሙ በሰላም ሚኒስቴርና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተጠኑ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱም የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎችና የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች፤ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ እስካሁን ለተከናወኑ ተግባራት ስኬታማነት ድርሻ ያበረከቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡