የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዛሬው ዕለት ማለትም በ15/04/2017 ዓ.ም በጋራ ባደረጉት የጋራ የትውውቅ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት በሀገራችን የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ለመቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ ከመቼውም በላይ በትጋትና በመቀራረብ እንደሚሰሩ ያረጋገጡ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ለትውውቅና ለመወያየት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ መምጣታቸውንና ላሳዩት የአመራር ትህትና ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ቤተ-ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግሰት ግንባታ ካላት የካበተና የዳበረ ልምድ በመነሳት በአሁኑ ሰዓት እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አገራዊ ፀሎት እንዲደረግ ጥሪያቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል እንደሚደረግ የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብርና በመደጋገፍ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡