የራስ ውስጣዊ ሰላም የአገር ሰላም መነሻ ነው!
የራስ ውስጣዊ ሰላም የአገር ሰላም መነሻ ነው!
ሰዎች ከራሳቸውና ከአካባቢያቸው ጋር ሰላም ኖሯቸው ለጋራ እድገትና አብሮ መኖር አስተዋጽኦ ካደረጉ ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ከፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኑሮ ባሻገር ሰዎች ከሰዎች፣ ከተፈጥሮና ከአካባቢ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ስለሚመለከት ሰላም ሁሉን አቀፍ ይዘት አለው፡፡
ሰላምን በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማኅበረሰብና በተቋም ደረጃ በማስረጽ፣ የዜጎችን፣ የወጣቶችን በጎፈቃደኝነትንና የመስጠት ዜግነታዊ ኃላፊነትን የህይወት ዘመን ባህል እንዲሆን በማድረግ፣ ማህበራዊ ሃብቶች፣ እሴቶችና ብሔራዊ ጥቅሞች በተልዕኮ ስምሪት ውስጥ ተካተው በመተግበር ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላምን የመገንባት ሥራ ማጠናከርን ይጠይቃል።
የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከታሪካዊ ቅራኔዎቻችን ይልቅ ለታሪካዊ መግባባታችን ቅድሚያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያ ሰላም፣ ፍቅርና ብልፅግና ትመኛለች፡፡ ለዚህ ምኞት ተግባራዊነትም ኢትዮጵያዊ በሙሉ እንደ እህትና እንደ ወንድም በአንድነት ለመነጋገር፣ ለመሥራት እንዲሁም በጋራ ለመጠቀም በንጹህ ልቦና መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የራስ ውስጣዊ ሰላም የአገር ሰላም መነሻ ነውና ሁላችንም ለሰላማችን ዘብ መቆም ይኖርብናል፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ!