የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ትውውቅ አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

May be an image of 7 people and textበትውውቅ ፕሮግራሙ ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ እንደተናገሩት የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ሰላማዊና የተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፆ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣይ በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተው የሰላም ሚኒስቴርም በትብብርና በቅንጅት ከካውንስሉ ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

May be an image of 5 people and textየኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ክቡር ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከመገፋፋት ይልቅ በመተባበር እና በመደጋገፍ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሃይማኖቶች ትልቅ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆያቸውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በሀገራችን ሰላም ጉዳይ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ፣የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባላት በትውውቅ ፕሮግራሙ ተገኝተዋል፡፡