ሙስና፣ ብልሹ አሠራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሀገር ሰላም ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳርፉ ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) ለሁለት ተከታታይ ቀናት "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ሃሳብ ለተቋሙ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የስልጠና መድረክ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ በመግባባት ተጠቃሏል።

May be an image of 2 people, newsroom and daisበሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልእክት “ሙስና ተለዋዋጭና የረቀቀ የአፈፃፀም ባህሪ ስላለው የተቀናጀ ትግል የሚጠይቅ ነው፤ ከቁሳዊና ቁሳዊ ያልሆኑ ሃብቶች ምዝበራ ባሻገር የሀገር ደህንነትንም ስለሚጎዳ የፀረ-ሙስና ትግል ከሰላም እና ከተቋማችን ተልዕኮ አንጻር የተለየ ባህሪ ይኖረዋል”፤ ብለዋል፡፡

“ሙስና ፍትህን የሚያዛባና የዜጎችን ነፃነት የሚጎዳ ወንጀል ስለሆነ ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሻገር የሚደረጉ ጥረቶችን በማገዝ ሁሉም ሚናውን መወጣት አለበት”፤ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

May be an image of 10 people and daisስልጠናው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል እንደሚያግዝ የገለጹት የስልጠናው ተሳታፊዎችም በሥነ-ምግባሩ አርዓያ የሆነ አመራርና ሠራተኛ በማፍራት የሥነ-ምግባር ጥሰት እንዳይፈፀም የአሠራር ሥርዓቱን ማዘመን፣ የሥነምግባር መመሪያዎችን ማሻሻል እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ማከናወን ችግሩን ለማቃለል የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተጠያቂነት አሠራርን የተከተለ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

May be an image of 8 peopleበተቋማት አመራሩንና ሠራተኛውን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ሥርዓት መፍጠር የተቋማትን ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን እንደሚያደርግ እና መልካም ስብዕና እንደሚገነባም ተመላክቷል፡፡

የሙስና ተጋለጭነትን ከፍ የሚያደርጉ በርካታ ጉዳዮች ስለመኖራቸው እና ችግሩን ለመግታትም በተቋማት በተቀናጀ መንገድ የሚደረጉ የትግል ስልቶችን በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡