በብሔረዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት የጥናት ውጤቶች ቀረቡ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) ብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን በማዳበር ብሔራዊ መግባባትና ሀገራዊ አንድነትን እንደሚያጎለብት ጥናቶች አረጋገጡ፡፡

ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በመደበኛና የክረምቱ ልዩ የበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች የተከናወኑ ተግባራት ማህበረ-ባህላዊ እሴቶችን በማጎልበትና በማሻሻል ሀገራዊ አንድነትን፣ ብሔራዊ መግባባትን እና ማህበረሰባዊ ትስስር እያጠናከረ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የተደረገው ጥናት አመላክቷል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ሀገራዊ ፕሮግራሙ ወጣቱን በማቀራረብ ዕርስ በርስ የሚያስተዋውቅ፤ በዜጎች መካከል የተፈጠረውን ጥርጣሬ በማጥፋት ከልዩነት ይልቅ አንድነትን እና ወሰን ተሻጋሪ አስተሳሰቦችን የሚያጎለብት፤ በሀገር ግንባታ ላይ የሚታዩ ስብራቶችን በመጠገን ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር በትልቁ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

May be an image of 1 person, studying, dais and newsroomMay be an image of 1 person and dais

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የመደበኛው መርሐ ግብር ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞች እና በክረምቱ ልዩ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት የሚሳተፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በአካባቢ የታጠረ እሳቤን ሰብረው ከተወለዱበትና ካደጉበት አካባቢ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት የኢትዮጵያዊ ብዝኃነት ፀጋዎቻችን የሆኑ ባህሎችን፣ ቋንቋዎችን፣ ማኅበራዊ እሴቶችን እና ወጎችን በመገንዘብ ርስ በራሳቸው የሚተዋወቁበትና የአብሮነት መስተጋብሮችን የሚያጠናክሩበት መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።May be an image of 3 people and newsroom

May be an image of 6 people and daisMay be an image of 2 people and dais

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የሰላም ሚኒስቴር ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሀገራዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን አፈጻፀም የሚያሳይ ጥናት ተሠርቶ የቀረበ ሲሆን በጥናቱ የተረጋገጠ ገንቢ ግኝት መሠረት ያደረገ አፈጻፀም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡