''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የሰላም ሩጫ በሰላም ተጠናቋል
Aplicações Aninhadas
Publicador de Conteúdos e Mídias
ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም. መነሻውን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በማድረግ በባምቢስ ፣ በዑራኤል አደባባይ ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ መጨረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው የሰላም ሩጫ ተጠናቋል።
በሰላም ሩጫው ላይ ክቡራን ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የውጭ ሁገር ዲፕሎማቶችና አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና የኃይማኖት አባቶች በሰላም ሩጫው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የሰላም ሩጫው ዓላማ በሀገራችን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም የበለጠ እንዲያጠናክር ለማድረግ እና መላው ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሰላም በጋራ እንዲሰሩ መነሳሳትን ለመፍጠር ያለመ ከመሆኑም ባሻገር እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም የምንሰጠውን ዋጋና ለሰላም ያለንን ፍላጎት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ መሆኑን ተገልጿል። በሩጫው በሴቶች እና በወንዶች ተወዳድረው 1-3 ላሸነፉ አትሌቶች ሽልማት ተበርክቶላቸል።
በመጨረሻ ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በኩል ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የሰላም ሩጫው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በተመረጡ ከተሞች ተካሂዷል።
Publicador de Conteúdos e Mídias
የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት
አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር
የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።
ተጨማሪAplicações Aninhadas
Publicador de Conteúdos e Mídias
ትንታኔ
በዓድዋ እሴቶች እየተገነባን የሀገራችንን ሰላም እናረጋግጣለን!!
የዓድዋ ድል ሉዓላዊነታችንን ያስከበርንበት፤ ወራሪ ጠላትን ያሳፈርንበት ታላቅ ድል በመሆኑ እየዘከርንና ታሪኩን በልኩ እያወሳን ለቀጣይ ትውልድ የማሻገር ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ታላቅ ድል እያንዳዳችን ልንማርባቸውና የዘወትር አስተሳሰብ ሊያደርጋቸው የሚገቡ በርካታ እሴቶች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ