አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር
አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር
የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት
የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።
የሰላም ሚኒስቴር ትኩረቱን አዎንታዊ ሰላም በማድረግ እንደ ሀገር የሰላም እሳቤ በትውልዱ አእምሮ ውስጥ እንዲሰርፅ እና ብሔራዊ መግባባት እንዲዳብር መንግስታዊ ከሆኑና ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር እና በቅንጅት ይሰራል፡፡
የሰላም ስራ በመንግስት ተቋም ብቻ ተከናውኖ የሚያበቃ ስራ አይደለም፡፡ የእያንዳንዱ ጠጠር ክምር ተራራ እንደሚሰራ ሁሉ እያንዳንዳችን ለሰላም የምንሰራው ስራ ተደምሮ የሀገርን ሰላም ያረጋግጣል፡፡ ሰላም ባለ ብዙ ባለቤት ነው፤ የሰላም ስራ የብዙሃንን ተሳትፎ ይጠይቃል። ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለማሻገር ትልቁ መሰረት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ህብረተሰቡ ያለውን ሚና በእጅጉ ከፍ ማድረግ ነው፡፡ ግለሰብ ሰላም ሲሆን ቤተሰብ ሰላም ይሆናል፤ የቤተሰብ ሰላም ለማህበረሰብ ይተርፋል፤ ማህበረሰብ ሰላም ሲሆን ደግሞ ሀገር ሰላም ትሆናለች፡፡