በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል ያለው ግንኙነት በህግና በአሰራር ሊደገፍ ይገባል ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር በመንግስታት ግንኙነት ፅንስ ሃሳብ እና አተገባበር ላይ ከፌዴራል ተቋማት ጋር ለሁለት ቀናት ያካሄደው ውይይት ተጠናቋል።

May be an image of 1 person and daisበመድረኩ ላይ ''የመንግስት ግንኙነት ፅንስ ሃሳብ፣አተገባበር እና የዓለም ተሞክሮ'' ፣ ''የኢትዮጵያ የመንግስታት ግንኙነት ህግ ማዕቀፍ'' ፣ ''በሰላም ሚኒስቴር እና የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮዎች የጋራ የሰላምና ጸጥታ የትብብር ቻርተር'' እና ''በመንግሥታት ግንኙነት ውስጥ የግጭት ተጋላጭነት ለመቀነስ መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች'' የተመለከቱ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ተቋማት አመራሮች የየራሳቸውን ተሞክሮ እና በቀጣይ ከተጠሪ ተቋማት እና ከክልል ቢሮዎች ጋር በቅንጅትና በትብብር ሊሰሯቸው ባቀዷቸው ተግባራት ላይ ውይይት አድርገዋል።

May be an image of 5 people, dais and textለተነሱ ሃሳቦች ማጠቃለያ የሰጡት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ አቶ ሀብታሙ ምትኩ የሰላም ሚኒስቴር በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል የግንኙነት ማዕከል ሆኖ እንዲሰራ በአዋጅ ተቀምጧል ያሉ ሲሆን ይህን ተግባር ለማከናወን የተለያዩ አሰራሮችን እና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ዴሞክራሲ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ወልዴ በበኩላቸው ''በሰላም ሚኒስቴር እና የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮዎች የጋራ የሰላምና ጸጥታ የትብብር ቻርተር'' ያስፈለገበት ምክንያት ስራዎች በትብብርና በአጋርነት እንዲሰሩ ነው ያሉ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር የመንግስታት ግንኙነት ውጤታማ እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከፌዴራል ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።