የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአካል በመገኘት ትውውቅ አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአካል ተገኝተው ከተቋሙ ኃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ ስለተደረገላቸው የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አመስግነው የኃይማኖት ተቋማት የሚያከናውኗቸው ተግባራት የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ የብዝሃ ኅይማኖት አማኒያን ሀገር በመሆኗ የሰላም ሚኒስቴር ይህን ምቹ ነባራዊ ሁኔታ ተጠቅሞ መንግስት በኃይማኖት፣ ኃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ ሳይገቡ በትብብርና በቅንጅት ከምንጊዜውም በላይ ለሰላም አብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የኃይማኖት ተቋማት የሰላም ጥሪዎች ፍሬያማ እንዲሆኑ እና ችግሮች በምክክርና በውይይት እንዲፈቱ በማድረግ የማይተካ ሚና ስላላቸው የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ እየፈታን ለነገው ትውልድ ሰላማዊና የበለፀገች ሀገር ለማስረከብ ዛሬ ትልቅ የጋራ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

May be an image of 1 person

May be an image of 7 people and textየኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በአካል ተገኝተው ትውውቅ ማድረጋቸውን አድንቀው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በሰላም ግንባታ ዙሪያ መስራታችን በሀገራችን ሰላም ግንባታ ሂደት የበኩላችንን ኃላፊነት ለመወጣት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡