‹‹የህልም ጉልበት ፤ ለእመርታ ዕድገት›› በሚል መሪ ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች ውይይት አደረጉ
‹‹የህልም ጉልበት ፤ ለእመርታ ዕድገት›› በሚል መሪ ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች ውይይት አደረጉ
‹‹የህልም ጉልበት ፤ ለእመርታ ዕድገት›› በሚል መሪ ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራ
ኅዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር፣ ‹‹የህልም ጉልበት ፤ ለእመርታ ዕድገት›› በሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ፡- አካታች፣ አሳታፊና ሁሉንም ዓይነት ኢትዮጵያዊ ብዝኃነቶችን ይዞ የተፈጠረ ሀገራዊና ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ፈተናዎች ተጋፍጦ ፈተናዎችን በድል አልፎ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና በዲፕሎማሲው ዘርፎች በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ፓርቲው ገና በተመሠረተ አጭር ጊዜ ውስጥ መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን መሥራቱን እና በመሥራት ሂደት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ዓይነተ ብዙ ዕምርታ እያስመዘገበ ያለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና የመሻገር ታላቅ ህልም ሰንቃ ለውጡን በመምራት ሁሉንም አካታች፣ ህብረ-ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት በለውጥ ንቅናቄ ውስጥ መሆኗን እና ይህንንም ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚፈፀሙ ተግባራትን አስመልከተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡