የግጭት ተጋላጭነት መመዘኛ ስታንዳርድ ተዘጋጀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር፤ ግጭቶች ከመፈጠራቸው በፊት ለመከላከል፣ መፍትሔ ለመስጠት እና የፈጣን ምላሽ አሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የግጭት ተጋላጭነት መመዘኛ ስታንዳርድ ተዘጋጅቷል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የግጭት ተጋላጭ አካባቢዎችን ለይቶ በተገቢ ሁኔታ በመሥራት ወደ ሰላም ቀጠና ለማሸጋገር የግጭት ተጋላጭነት መመዘኛ ማዘጋጅት አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መመዘኛ ስታንዳርዱ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጃፈር በድሩ፡- ለግጭት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን የተጋላጭ ደረጃ የሚያሳይ የመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) መዘጋጀቱ ግጭትን ቀድሞ ለመከላከል ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ምክንያታዊ፣ ገለልተኛ እና ሳይንሳዊ እሳቢዎች ያካተተ ሆኖ ልምድ ባካበቱ ምሁራን ጥናት እና ምርምር መዘጋጀቱን አሳውቀዋል፡፡

 

 

 

 

 

ግጭት እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ፤ ወቅት እና አውድ የተለያዩ አመላካች ሊኖረው ስለሚችል በመመዘኛ ስታንዳርድ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ ከመፈጠሩ በፊት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚቻልበትን ሥርዓት ለመፍጠር ታስቦ ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና ከጀስቲስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የግጭት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይርጋለም መንግሥቱ ገልጸዋል፡፡