የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችን ተቀብለው አነጋገሩ

ኀዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል ውይይት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች ጋር አድርጓል።
ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የሰላም ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በራሳቸው ፈቃድ ተሳትፎና ፍላጎት ባረጋገጠ መልኩ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።.
ክቡር አቶ ቸሩጌታ አክለውም በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ 3.1 ሚሊዩን ዜጎች መኖራቸውን ገልፀው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ሥራ ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ከተባበሩት መንግስታት የመጡት የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው በቀጣይ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።