ሀገራዊ የሰላም ምክክር ኮንፈረንስ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አመታዊ ሀገራዊ የሰላም ምክክር ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በመድረኩም ከአስራ ሁለቱም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የተወጣጡ የፀጥታ መዋቅር ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትር ድኤታዎች፣ የሐገር ሽማግልዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኘተዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በመድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የሲዳማ ክልል ለሁሉም ክልሎች አርአያ የሆነ ክልል በመሆኑ ህዝቡ እንዲሁም እንግዶች በሠላም ወቶ የሚገባበት መሆኑን ገልፀዋል።

ሲዳማን የሰላም ደሴት ማድረግ ችለናል ያሉት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፀጥታ ስራን ለማረጋገጥ ሁሌም በመስራት የህብረተሰቡን ደህንንነት በማስጠበቅ ከፀጥታ ስጋት ነፀ የሆነ ክልል መፍጠር እንደተቻለም ገልፀዋል።

አክለውም በክልሉ ለሰፈነው አስተማማኝ ሰላም የፀጥታ ተቋማት፣ ፖሊስና ህብረተሰቡ አንድ በመሆን በተሰራ ሥራ የመጣ ውጤት እንደሆነ አመላክተው ሰላምን በቋሚነት ለማጽናት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተቋማትን ከማዘመን ባሻገር ፖሊስ ህብረተሰቡን በቅርበት እንዲያገለግልና ምቹ የስራ አካባቢ እንዲኖረው ህዝብን በማነቃነቅ ስራ መሠራቱን ጠቁመዋል።

አያይዘውም አለም በደረሰበት የወንጀል መከላከል ስልት መሰረት በሐዋሳ ከተማ ላይ ከሰው ሃይል ባለፈ በቴክኖሎጂዎች የታገዘ ሰላም የማስከበር ስራ በሰፊው እንደተሠራም ተናግረዋል።

በመድረኩም ፖሊሳዊ ስነ-ምግባርን በመላበስ የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ በክልሉ የተለዩ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መመሪያ፣ የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን እና የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ ጽህፈት ቤቶች ባስመዘገቡት ውጤት እውቅና እንዲሁም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።