17ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) 17ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት “ሰንደቅ ዓላማችን የነፃነታችንና የብሔራዊ ክብራችን ምልክት፣ የኅብረብሔራዊ አንድነታችንና እኩልነታችን መገለጫ፣ የትናንት ተጋድሏችንና መስዋዕትነታችን ከዛሬ ሉዓላዊነታችን፤ የዛሬ ሉዓላዊነታችንን ደግሞ ከነገ ተስፋችንና ህልማችን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው” ፤ ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ “የነገ ህልማችን ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ልዕልናችንን ማረጋገጥ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አፍሪካዊት ሀገር መገንባት ነውና የዛሬውን ሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ለህልማችን መሳካት በጋራ ቃላችንን የምናድስበት ቀን መሆን ይኖርበታል” ፤ ሲሉም አክለዋል::May be an image of 6 people, crowd and text

የዘንድሮው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቱ ያሉ ዜጎች በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው ቃለ መሃላ በመፈፀም ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ዳግም በመግለጽ የሀገራችንን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ቃላቸውን የሚያድሱበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !